ከምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉ ወገኖች ላለፉት አራት አመታት በአስከፊ ችግር ላይ ወድቀው ይገኛሉ። እነዚህ ወገኖች የፌደራል መንግስት ወደ ቀያቸው ሊመልሳቸው ይገባል።

የወልቃይት ጉዳይ ለብቻው ተነጥሎ ‘አከራካሪ ቦታዎች’ ተብሎ ሊጠራ አይገባም። ለኔ ይገባኛል የሚሉ ጥያቄዎች በመላ ኢትዮጵያ አሉ ነገር ግን ‘አከራካሪ ቦታዎች’ ተብለው አይጠሩም ። ለምሳሌ ፥ የአዲስ አበባ ጉደይ፣ የመተከል ጉዳይ፣ በሱማሌ እና አፋር አዋሳኝ ቦታ ያለው ጉደይ፣ በኦሮሚያ እና በሱማሊያ አዋሳኝ ቦታዎች ያለ ጉዳይ ማንሳት ይቻላል።

ህገመንግስቱ እስካልፈረሰ ድረስ በህገምንግስቱ መሰረት ምዕራብ ትግራይ “አከራካሪ ቦታዎች” ተብሎ ሊጠራ አይገባም። ስለዚህ ህገመንግስቱ ለአንዱ ጉዳይ የሚሰራ ለሌላው የማይሰራ ሊሆን አይችልም።

የፌደራል መንግስት ፥ ምዕራብ ትግራይ ከዚህ በፊት እንደነበረበት ወደ ትግራይ ክልል በመመለስ እና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ የፕሪቶሪያን ውል ሙሉ በሙሉ በመፈፀም ግዴታው ይወጣ።

#ይበቃል

#ተፈናቃዮች_ወደ_ቀያቸው_ይመለሱ

admin
Author: admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *